የመስቀል ደመራ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ ነው።

55

ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የመስቀል ደመራ በዓል በባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ኀላፊዎች እና የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

አሁን ላይ ስብከት በሰባኪያን ቀርቦ፣ ከደመራው መለኮስ በፊት መዝሙር በዘማሪያን እየቀረበ ነው።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የሃይማኖቱ ታላላቅ አባቶች፣ ቀሳውስት፣ የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች እና ምዕመናን ተገኝተው በዓሉ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ከደቂቃዎች በኃላም የተዘጋጀው ደመራ ይለኮሳል፡፡ ተከትሎ ሌሎች የሃይማኖቱ ሥርዓት እንደሚከናወን ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሻምፒዮናው ለሀገራችን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ተዘጋጅተናል” አትሌቶች
Next article“የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች በኢትዮጵያ የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጎ እየተሠራ ነው” የቱሪዝም ሚኒስቴር