በሥድስት ወራት ብቻ በዞኑ በትራፊክ አደጋ የ83 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረትም ወድሟል፡፡

259

ባሕር ዳር፡- ጥር 18/2012ዓ.ም (አብመድ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ሥድስት ወራት የተከሰተው የትራፊክ አደጋ ከአምናው በ12 በመቶ መጨመሩን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በመምሪያው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንዳስታወቁት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ባለፉት ሥድስት ወራት 148 የትራፊክ አደጋዎች ደርሰዋል፤ በዚህም የ83 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዬን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል፡፡ የደረሰው የትራፊክ አደጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ12 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ነው ያስታወቁት፡፡

ከልክ በላይ ፍጥነት፣ ከመጠን በላይ ጭነትና የእግረኛች የመንገድ አጠቃቀም ጉድለት ለአደጋው መከሰት በቀዳሚነት እንደሚጠቀሱ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ አስታውቀዋል፡፡

በሥድስት ወራት የመንገድ ደኅንነት ህጉን የተላለፉ 24 ሽህ 114 ሾፌሮች፣ ረዳቶች፣ ባለሃብቶችና እግረኞች ክስ ተመሥርቶባቸው መቀጣታቸውንና ከዚህም ከ5 ሚሊዬን 300 ሽህ ብር በላይ ወደ መንግስት ካዘና ገቢ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

መረጃው የጋሻዬ ጌታሁን ነው፡፡

Previous articleበእስራኤል የኢትዮጵያን ቡና ለማስተዋወቅ የሚያስችል አውደ ርዕይ ተካሄደ፡፡
Next article“የአጋቾችን ማንነት፣ ያገቱበትን ምክንያት እና እንዴትና ለምን ታገቱ? የሚለውን ጉዳይ ለማወቅ ከፍተኛ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ በቅንጅት እየተሠራ ነው፡፡” የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን