
ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት መጠናከር እንዳለበት አምባሳደር ረታ ዓለሙ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያን ቡና በእስራኤል ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው አውደ ርዕይና የምክክር መድረክ ትናንት ጥር 17 ቀን 2012 ዓ.ም በቴል አቪቭ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ውስጥ ተካሂዷል፡፡
የመርሀ ግብሩ ዓላማ በእስራኤል የኢትዮጵያን ቡና ማስተዋወቅ እና በሁለቱ ሀገራት የቡና ኩባንያዎች መካከል ትስስር መፍጠር ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እንዳሰታወቀው በመርሀ ግብሩ ባህላዊ የቡና ማፍላት ሥነ ስርዓት፣ አውደ ርዕይ እና የቢዝነስ ኮንፈረንስ ተካትተዋል፡፡
በእስራኤል የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በንግድና ኢንቨስትመንት መጠናከር እንዳለበት ተናግረዋል።
በቡና ምክክር መድረከ ላይ አምባሳደሮች፣ በእስራኤል የሚገኙ የቡና አስመጪዎች እና ነጋዴዎች፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ የቡና ላኪዎች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ የቤተ እስራኤላውያን ማኅበረሰብ አባላት፣ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።