“የመስቀል ዋና መልዕክቱ ጥላቻን መግደል ነው” ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የሥነመለኮት መምህር

42

ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመስቀል ዋና መልዕክቱ ጥላቻን መግደል በመሆኑ በዓሉን ለሰው ልጅ ሰላም ክብር እና ፍቅር በማሰብ ልናከብረው ይገባል ሲሉ የሥነመለኮት መምህሩ ዳንኤል ሰይፈሚካኤል አስገንዝበዋል።

የደመራ በዓልም የእኩልነት፣ የሰላም እና የነጻነት በዓል እንደመሆኑ በሕይወት አኗኗርም ሆነ በበዓሉ አከባበር ታሪካዊ አውዱን የሚመጥን መንፈሳዊ ገጽታ መላበስ እንደሚገባ አሳስበዋል።

መምህር ዳንኤል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መስቀሉ የአሸናፊነት፣ የነጻነትና የሰላም ምልክት ነው። ነገረ መስቀሉ ጳውሎስ ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ግን ሕይወት ነው ብሎ የተናገረው መልእክቱ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን በመስቀል በከፈለው መስዋዕትነት ተለያይተው የነበሩ ሰውና ፈጣሪ አንድ ያደረገበት እንደመሆኑ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የመስዋዕትነት፣ የሉዓላዊነት እና የሕይወት ምልክት ነው።

በዓሉን ከዋናው መልእክት በተቃራኒ ሆኖ ማክበር አይቻልም። መስቀል ዋና መልእክቱ ጥላቻን መግደል ነው። ለሰው ልጅ ሰላም ክብር እና ፍቅር በማሰብ መሆን መከበር ይገባዋል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article1 ሺህ 498ኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በታላቁ አንዋር መስጅድ እየተከበረ ነው።
Next articleየመውሊድ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ መጂት መስጅድ እየተከበረ ነው።