
ባሕር ዳር: መስከረም 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በሐረሪ ክልል 1498ኛው የመውሊድ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ በሀረር ከተማ ሸዋበር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች በመከበር ላይ ነው።
ኢዜአ እንደዘገበው በበዓሉ ላይ የታደሙ የእምነቱ ተከታዮች እንደገለጹት የመውሊድ በዓል ላይ የነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መልካም ተግባራት የሕይወት መርሕ በማድረግ በዓሉን ማክበር ይገባል ብለዋል።
የመውሊድ በዓልን ሰላምን፣ በጎነትንና አብሮነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማከናወን እንደሚያከብሩትም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!