ከሰሞኑ በተፈጠረው የፀጥታ አለመረጋጋት የንብረት ውድመት መድረሱን የአንኮበር ወረዳ ገለጸ፡፡

38

ደብረ ብርሃን፡ መስከረም 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአንኮበር ወረዳ አሥተዳዳሪ ታደሰ ፈቅይበሉ እንዳሉት ከሰሞኑ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ከፍተኛ የንብረት ውድመትና ዘረፋ ተፈጽሞባቸዋል።

በተጨማሪም የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ድርጅት ንብረት የኾኑ ተሽከርካሪዎችም ተዘርፈዋል ብለዋል።

የወረዳ አሥተዳደሩን ተቋማት በአጭር ጊዜ ሥራ ለማስጀመር አስቸጋሪ በኾነ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አቶ ታደሰ ገልጸዋል።

የጉዳት መጠኑን ለመለየት ኮሚቴ እየተዋቀረ ስለመኾኑም አስረድተዋል።

ዘጋቢ፡- ለዓለም ለይኩን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢስላም- የዓለም ሰላም!
Next article“በአማራ ክልል የመስቀልና የመውሊድ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ተደርጓል” ኮማንድ ፖስት