
ባሕር ዳር: መስከረም 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ለ12 ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች ሥልጠና በስኬት መጠናቀቁን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ አስታወቁ፡፡
ሥልጠናው የውስጠ ፓርቲ አንድነትን የበለጠ ያጠናከረ፣ አመራሩ እንዲማማርና ተሞክሮ እንዲለዋወጥ የረዳ መኾኑን አቶ አደም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የፓርቲውን መሰረታዊ እሳቤዎች መነሻ በማድረግ ተለዋዋጭ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት መድረክ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በአጠቃላይ እቅዶቻችንንና ለሕዝብ ቃል የገባነውን በውጤታማነት እንድንፈፅም የሚያስችለን መድረክ ነው ብለዋል አቶ አደም፡፡
ለስልጠናው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!