የ2015/16 ዓ.ም የምርት ዘመን የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

69

ባሕርዳር፡ መስከረም 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በግብርና ሚኒስቴር በ2015/16 ዓ.ም ምርት ዘመን በመኸር እርሻ 17 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በማልማት 513 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ከክልሎች ጋር በቅንጀት እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

ወቅታዊ የመኸር እርሻ ሥራ ሁኔታን በተመለከተ የሰብል ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ለማ እንደገለጹት በኦሮሚያ፣ በአማራ ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ትግራይ እና ሐረሪ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 17 ሚሊዮን 390 ሺህ 818 ሔክታር መሬት ለማረስ ታቅዶ እስከ አሁን በባህላዊ 14 ሚሊዮን 137 ሺህ 156 ሔክታር እና በትራክተር 3 ሚሊዮን 960 ሺህ 990 ሔክታር፤ በድምሩ 18 ሚሊዮን 98 ሺህ 146 ሔክታር መሬት ታርሷል።

ከታረሰው እርሻ መሬትም 16 ሚሊዮን 578 ሺህ 415 ሔክታር (95%) በዘር ተሸፍኗል።

በዘር ከተሸፈነው 16 ሚሊዮን 578 ሺህ 415 ሔክታር ውስጥ 8 ሚሊዮን 280 ሺህ 741 ሔክታር በክላስተር (በኩታ ገጠም እርሻ) በዘር የተሸፈነ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በሰብል ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል አርሶ አደሩ በቀበሌው ካሉ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ጋር በቅርበት በመሥራት የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራ መሥራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመውሊድ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበርበት ቦታ – ጀማ ንጉሥ
Next article“የመውሊድ በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ፣ በመደጋገፍ ሰላምና አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል” የሃይማኖት አባቶች