
ባሕር ዳር: መስከረም 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሙስሊሙ ሕብረተሰብ በዓሉን ለማክበር ሲሰባሰብ በተለመደው የኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባህርይ የመከባበርና የመረዳዳት ባህሉ ሊሆን ይገባል።
እስልምና ሠላምን የሚሠብክ እምነት ከመሆኑ አንጻር የእምነቱ ተከታዮች ከምንጊዜውም በላይ ለሀገራችን ዘላቂ ሠላም የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሃይማኖት አባቶች አስተምህሮቱን ለማጠናከር ጥረት እንዲያደርጉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል እመኛለሁ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!