
ባሕርዳር፡ መስከረም 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሐምሌ 1/2015 እስከ መስከረም 8/2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ 401 ሺ 830 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦን ላይን መስጠቱን አስታውቋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሐምሌ1/2015 ዓ.ም ጀምሮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጡን በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦን ላይን ማድረጉ ይታወሳል።
በዚህም ከፌደራል እስከ ክልል ባሉት የንግድ ተቋማትና መዋቅሮች 401 ሺ 830 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦን ላይን ተሰጥቷል። ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባወጣው መረጃ በኦንላይን ከተሰጡ የአገልግሎት የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ የንግድ ሥራ ፈቃድ ስረዛ፣ የንግድ ስም ማሻሻያ እና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆኑ አገልግሎቱ በኦን ላይን በመሰጠቱ የተገልጋዮችን እንግልት ማስቀረት፣ ወጪ እና ጊዜያቸውንም በመቆጠብ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ተችሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!