የደሴ ከተማ የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ54ሺ በላይ ተማሪዎችን በይፋ ማስተማር ጀመረ።

53

ባሕር ዳር: መስከረም 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የ2016 ዓም የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤት በይፋ ተጀምሯል።

የትምህርት አከፋፈቱም በተስፋ ድርጅት አጠቃላይ አንደኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን፣ የመምሪያና ክፍለከተማ የሥራ ኀላፊዎች እና ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተገኝተው አስጀምረዋል።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ፍቅር አበበ በ52 የመንግሥትና በ12 የግል ትምህርት ቤት ከ64ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለመመዝገብ ታቅዶ ከ54ሺ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው የማስተማር ሥራው መጀመሩን ተናግረዋል። በደሴ ከተማ ከ7ሺ በላይ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለኾኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉም ተገልጿል።

የመምሪያው ባለሙያዎች በሁሉም ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ ክፍሎቹን በማዘጋጀት አስፈላጊውን የማስተማሪያ ቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል ። እንደ ደሴ ከተማ ከባለፈው ዓመት የተሻለ የመማሪያ መጽሐፍት ቢኖሩም ከፍተኛ የመጽሐፍት እጥረት እንዳለ ገልጸዋል።

የተስፋ ድርጅት አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ ተስፋየ መከተ በ2016 የትምህርት ዘመን በቅድመ ዝግጅት የመማሪያ ክፍሎችና ወንበሮችን በማደስና ምዝገባ በማካሄድ በትምህርት ቤቱ ለ750 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የጽሕፈት መሳሪያ፣ ዩኒፎርምና የምገባ ድጋፍ በማድረግ ይጀመራል ብለዋል።

የካራጉቱ የመጀመሪያና መካከለኛ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር ወርቁ መሐመድ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የእቅዱን መቶ በመቶ መዝግቦ በሁለት ፈረቃ እንዲማሩ አድርጓል ብለዋል።

ከደሴ ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በዘንድሮው የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሁሉም ተማሪ የተሻለ የማለፊያ ውጤት ሲያመጡ ከክልሉ ከፍተኛ ውጤታማ ያስመዘገቡትም የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው ብለዋል። በቀጣይም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት እና አዲስ በሚከፈተው በመምህር አካለ ወልድ በስፔሻል ክፍል በርካታ ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንደሚኾኑም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ወደ ሰላም ከፍታ ለመሻገር የሁላችን ርብርብ እና መደማመጥ ያስፈልጋል” ኮሎኔል ኤፍሬም ተስፋየ
Next articleበደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ስር የሚገኙ 81 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ዛሬ ጀመሩ።