“በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ ተጀምሯል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ

52

ባሕር ዳር: መስከረም 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በ2016. ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ ዛሬ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት መጀመሩን በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

በዞኑ 158 የአንደኛ ደረጃ እና 22 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር መጀመራቸውን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ገብረ ማርያም መንግሥቴ ገልጸዋል።

በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመጽሐፍ አቅርቦትን በማሟላት ለተማሪዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ያነሱት አቶ ገብረ ማርያም መምህራን በቂ ዝግጅት በማድረግ ለተማሪዎች ዕውቀትን በማስጨበጥ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትኩረት እየተሠራ እንደኾነም አንስተዋል።

አጋዥ ለሌላቸውና የአቅም ችግር ላለባቸው ተማሪዎች 2 ሺህ 480 ደርዘን የደብተር ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመውሊድ በዓል ረቡዕ መስከረም 16/2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ተገለጸ።
Next article” 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበዋል፣ የዓመቱ መደበኛ ትምህርትም ተጀምሯል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ