
ባሕር ዳር: መስከረም 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ከእቅዱ በላይ የሥራ እድል መፍጠሩን ገልጿል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ ፦
👉 ለ1 ሚሊዮን 203 ሺህ 180  ዜጎች  የሥራ እድል ለመፍጠር  አቅዶ  ነበር።
👉 ለ1 ሚሊዮን 264 ሺህ 131 ዜጎች የሥራ እድል  መፍጠር ችሏል።
👉 ከዚህ   ውስጥ  ደግሞ 876 ሺህ 619 ቋሚ የሥራ እድል የተፈጠረላቸው ናቸው።
👉  5 ሺህ 184  ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት የሥራ እድል  ተፈጥሮላቸዋል ተብሏል። በክልሉ የነበረው ሰላም ለክንውኑ መሳካት አንዱ ምክንያት እንደኾነም ተነስቷል። 
የፌዴራል ሥራ እና  ክህሎት ሚኒስቴር  የሥራ እድል ፈጠራን አስመልክቶ  በሦስተኛ ወገን በሀገር አቀፍ ደረጃ ባስጠናው ጥናት በአማራ ክልል የሥራ እድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች ውስጥ 93 ነጥብ 6 በመቶ ውጤታማ መኾኑን  ማረጋገጡን ገልጸዋል።  ይህም ክልሉ  በሀገር አቀፍ ደረጃ  የተሻለ አፈጻጸም  ማሳየቱን  አንስተዋል።
በበጀት ዓመቱ፦ 
 👉  የሥራ እድል ለተፈጠረላቸው ዜጎች  6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የገበያ ትስስር  ተፈጥሮላቸዋል።
👉 4  ቢሊዮን ብር መደበኛና ተዘዋዋሪ ብድር ተሠራጭቷል። 
የሚገነቡ ሸዶችም የውኃ፣ የመብራት፣ የመንገድ እና መሰል መሠረተ ልማቶች ማሟላት አንዱ የትኩረት አካል ቢኾንም አሁንም ችግሮች መኖራቸውን አንስተዋል። በዚህ በጀት ዓመት ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት መደረጉንም አንስተዋል። የክልሉ ሰላም ወደ ነበረበት ከተመለሰ የወጣቶችን የኢኮኖሚ ችግር ለመፍታት መንግሥት ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል ኀላፊው።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
 
             
  
		