
ባሕር ዳር: መስከረም 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ ክብረ ወሰኑን ሰበረች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በብሪጅድ ኮስጊ በ2019 የችካጎ ማራቶን የተያዘውን ክብረ ወሰን ነው። ክብረ ወሰኑ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ 04 ሰከንድ ነበር። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት 2 ሰዓት 11 ደቂቃ 53 በመግባት ነው ክብረ ወሰኑን ያሻሻለችው። ትዕግሥት አሰፋ ክብረ ወሰን የሰበረችበት የማራቶን ውድድር በበርሊን ሁለተኛ ድሏ ኾኖ ተመዝግቧል።
በወንዶች የበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ታደሰ ታከለ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። ኬኒያዊው አትሌት ኬፕቾጌ አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!