
ባሕር ዳር: መስከረም 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በ2023/24 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ የግብጹ አል አህሊ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ 11 ጊዜ አሸናፊ በመኾን የተለየ ሥም እና ዝና አለው፡፡ አል አህሊ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግም አሸናፊ ነው።
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ 75 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የካይሮ ዓለምአቀፍ ስታዲየም ይከናወናል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዛንዚባሩን ኬ ኤም ኬ ኤም ክለብን በደርሶ መልስ 5 ለ 2 በኾነ ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ፈረሰኞቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ አል አህሊን ማሸነፍ ከቻሉ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባታቸውን ያረጋግጣሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!