
ባሕር ዳር: መስከረም 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ”መስቀል በጉራጌ ዞናዊ ፌስቲቫል” በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ ተክለሃይማኖት ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል። የጉራጌ ዞን አሥተዳደር፣ የጉራጌ ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ፣ የጉራጌ ልማትና ባሕል ማኅበር እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች ናቸው።
”መስቀል በጉራጌ ”ከበዓል ባለፈ የቱሪስት መስህብ በማድረግ ለኢኮኖሚ ምንጭነት ለማዋል እየተሠራ መኾኑን ነው የዞኑ አሥተዳደር የገለጸው። የዞኑን ልማት ከፍ በማድረግ የጉራጌ ብሔርን ሀገር በቀል እውቀት ለትውልድ ማሻገር እንደሚያስፈልግም የዞኑ አሥተዳደር ጥሪ አቅርቧል። በመድረኩ የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ የጉራጌ ዞን አሥተዳደር ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የጉራጌ ማኅብረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!