
ባሕርዳር፡ መስከረም 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ዘርፈ-ብዙ ትብብር ለማሳደግም ተስማምተዋል።
ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን በያዝነው የፈረንጆቹ አመት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ሚና በተመለከተ ገለፃ ማድረጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒውዮርክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!