“ሁሉም የመስቀል ደመራ በዓል የሰላም አምባሳደር ሊሆን ይገባል” የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ

90

አዲስ አበባ፡ መስከረም 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመስቀል ደመራ በዓል የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የፍቅር መገለጫ በዓልነቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ኅላፊነቱን መወጣት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳስቧል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አዘጋጅነት የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በውይይቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ገዳማት እና አድባራት የተውጣጡ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰብሳቢ መጋቢ ታምራት አበጋዝ የመስቀል ደመራ በዓል የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የፍቅር መገለጫ በዓልነቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅዖ መወጣት አለበት ብለዋም።

የመስቀል ደመራ በዓል ከእምነቱ ተከታዮችና ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የዓለም ቅርስ ኾኗል ያሉት የጉባዔው ሰብሳቢ መጋቤ ታምራት አበጋዝ “ሁሉም የመስቀል ደመራ በዓል የሰላም አምባሳደር ሊሆን ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ብርሃን ከተማ መሠረት ልማት መምሪያ በተያዘው በጀት ዓመት በ721 ሚሊየን ብር የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንደሚሠሩ አስታወቀ።
Next article“በአማራ ክልል ከመስኖ ልማት 40 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰብል ምርት ለማግኘት ታቅዷል” ግበርና ቢሮ