
ባሕር ዳር: መስከረም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል መረጃ ነው ተብሎ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኮረና ቫይረስ ክትባቶች የህጻናት እና ወጣቶችን ሞት የማይከላከሉ እና ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ናቸው።
አሶሽየትድ ፕሬስ ባጣራው መረጃ ደግሞ የቅርብ ጊዜ የCDC መረጃ እንደሚያመለክተው በሽታው ራሱ የመግደል አቅሙ እየደከመ ስለሆነ ክትባቱ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ሞት ለመከላከል ምንም አይነት ሚና መጫወቱን አያመለክትም፡፡
ነገር ግን መረጃው እንደሚያሳየው ክትባቱ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ህጻናት እና ወጣቶች ሆስፒታል ለመተኛት የሚያደርሳቸው ከባድ ምልክቶች እየታየባቸው አይደለም፡፡
ከዚህም በላይ “ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች” ተብለው በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የወጡት እንደ ትኩሳት፤ ሙቀት እና እብጠት ጋር የተያያዘ ህመም፣ ምቾት መንሳት እና ሌሎች ምልክቶች የበሽታው እንጂ የክትባቱ አይደሉም፡፡
እነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ መረጃዎች የሚያሳያዩት ኮረና ቫይረስ ክትባት ከበሽታው ካለማዳኑም በላይ፣ ከፍተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላሉ፡፡
ብዙ ሰዎችም ይህ መረጃ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል(CDC) ነው ብለው ሲያጋሩት ታይቷል፡፡ የCDC መረጃ እንደሚያመለክተው ግን በተፈጥሮ ህጻናት እና ወጣቶች በሌሎች የዕድሜ ክልል ከሚገኙት ጋር ሲነጻጸሩ ኮረና ቫይረስ የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ ስለሆነ ክትባቱ ያለው ተጽእኖ ዝቅተኛ ነው፡፡
ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአሜሪካ በበሽታው የሞቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ከ1 በመቶ ያነሱ መሆናቸውን የሲዲሲ መረጃ ያሳያል።
“በእርግጥ የሞት መጠን በጣም ዝቅተኛ በሆነበት ሁኔታ በክትባቱ ምክንያት የቀነሰው የሟቾች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ መሆኑ አያስገርምም” ሲሉ በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የጤና ጥበቃ ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ አሜሽ አዳልጃ ገልጸዋል፡፡ መረጃው የኢቢሲ ፋክት ነው::
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!