
ባሕር ዳር: መስከረም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ውይይቱ እየተካሄደ ያለው “ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የሁሉንም አካል ርብርብ ይጠይቃል” በሚል መሪ መልእክት ነው።
በውይይት መድረኩ የባሕርዳርና አካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጄኔራል ሙሉአለም አድማሱ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጊዜው ታከለ ባቀረቡት ጽሑፍ በነበረው የጸጥታ ችግር ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ችግሮቹ በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት የሚፈቱ ናቸው ያሉት ጽሑፍ አቅራቢው፤ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ችግሮች እንዲፈቱ ከሕዝቡ ጋር እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል።
የውይይቱ ዓላማ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የሕዝቡን ተሳትፎ ለማጠናከር መሆኑን አስታውቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!