
አዲስ አበባ: መስከረም 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማኅበር 16ኛው ዓመታዊ ጉባኤውን ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ አባላት ጋር በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።
በጉባኤው ላይ የተገኙት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሲራጅ አህመድ ማኅበሩን በማሳደግ የአንስቴዥያ ህክምናን በጥራት እና በምቾች ለተገልጋዮች እንዲደርስ ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የትምህርት አሰጣጡን ከፍ ለማድረግ የትምህርት ቀረጻ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ተናግረዋል።
አሁን ላይ የአንስቴዥያ (የሰመመን) ህክምና ተፈላጊ በመኾኑ በተገቢው መንገድ ለታካሚዎች እንዲሰጥ ማኅበሩ ለባለሙያዎችና ለተማሪዎች ለሥራ አጋዥ የሚኾኑ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።
በቀጣይም የአንስቴዥያን ህክምና በማሻሻል በጥራት ለታካሚዎች ለማድረስ ለባለሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት ማኅበሩ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ለማኅበሩ ትብብር ያደረጉ እና በሙያቸው በተገቢው መንገድ ህክምናውን ለታካሚዎች ያደረሱ አጋሮችን እና በአንስቴዥያ የትምህርት ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተመሪዎችም ተሸልመዋል።
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!