ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።

46

ባሕር ዳር: መስከረም 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ቀን 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያካሂዳል።

በአሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ 26 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን ከጳጉሜን 3 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያደርግ ቆይቷል።

ከሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋርም የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችሲያደርግ የቆየው ብሔራዊ ቡድኑ÷ ለዛሬው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ማከናወኑ የሚታወስ ነው፡፡

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በሁለቱ ሀገራት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ስምምነት መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል መባሉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ ካሸነፉ በቀጣዩ ዙር ከኡጋንዳና አልጄሪያ አሸናፊ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጥላቻ ንግግር ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ ምስቅልቅሎችን እያስከተለ ነው።
Next article“የኮሌራ ክትባትን 98 በመቶ መስጠት ተችሏል” የደቡብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ