
ባሕርዳር፡ መስከረም 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 78ተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሰላም ፣ብልፅግና፣ ለውጥ እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዮርክ መካሄዱን ቀጥሏል።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጉባኤው ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ በባለ ብዙ ወገን የትብብር ስርዓት ውስጥ ቁልፍ ሚና የምትጫወት አገር መሆኗን የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገልጸዋል፡፡
ጉቴሬዝ በስልጣን ዘመናቸው ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አመላክተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሰላም ስምምነቱን ትግበራ አስመልክቶ ገለጻ ማድረጋቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!