የማኅበራዊ ሚዲያውን ዕድገት ተከትሎ ሀሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተሠራጩ መሆኑ ተገለጸ።

28

ባሕር ዳር: መስከረም 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሁን ላይ የማኅበራዊ ሚዲያውን ዕድገት ተከትሎ ሀሰተኛ መረጃዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተሠራጩ ነው። ሀሰተኛ መረጃ የሌለን ነገር አንዳለ አድርጎ በማቅረብ፣ እውነትን በማዛባት እንዲሁም ሌላ እውነት በመፍጠር አለመተማመንና ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ነው ያሉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት መምህር ሙሉቀን አሰግደው(ዶ.ር) ናቸው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን መሰል መረጃዎችን ለማስተባበል በቅድሚያ ራሳቸው ተዓማኒ መሆንና ከሀሰተኛ መረጃው በተቃራኒ ያለውን እውነት ሊነግሩ የግድ ነው ብለዋል መምህሩ። ለዚህ ደግሞ የይዘት ጫና ሳይኖር መስራት እና ለሀቅ ማጣራት ስራ ብቁ የሰው ኀይልና የቴክኖሎጂ ዝግጅት ሊኖራቸው የግድ ነው ተብሏል። ሀሰተኛ መረጃ ሰጪዎች የማኅበረሰቡን መረጃ የማጣራት እና የማመሳከር ልምድ ማነስ እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ነው የሚሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሙኒኬሽን ትምህርት መምህሩ እያዩ አለማየሁ ናቸው።

አሁን ላይ መረጃ የሁሉም ነገር መሰረት ነው የሚሉት መምህራኑ የዜጎችን የመረጃ ግንዛቤ ለማሳደግ በስርዓተ ትምህርት ጭምር እንዲሰጥ መክረዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ኤም አዲስ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በምርት ዘመኑ በምግብ ራስን መቻል ፣ ለኢንዱስትሪዎች ጥሬ እቃ ማቅረብ እና ገበያ ተኮር ሰብሎች ላይ ትኩረት ተደርጓል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next article“ከ51 ሺህ በላይ ከስደት ተመላሾች ሥልጠና ወስደው ወደ ሥራ ሊሰማሩ ነው” የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር