
ባሕርዳር፡ መስከረም 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመርያ ዙር ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ የሚያደርጉት ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ሁለቱ ፌዴሬሽኖች ባደረጉት ስምምነት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መግለጹን ጠቁሟል።
በስምምነቱ መሰረት የመጀመርያው ጨዋታ ዓርብ መስከረም 11 ፣ የመልስ ጨዋታ ማክሰኞ መስከረም 15/2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚከናወን መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!