የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የትምህርት ካላንደርን ይፋ አደረገ፡፡

444

ባሕርዳር፡ መስከረም 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር አጠቀላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ካላንደርን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉም ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቀዋል፡፡

ከመስከረም 2 እስከ 6/2016 ዓ.ም ለመምህራን እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትውውቅይ ይደረጋል፡፡

ከመስከረም 7 እስከ 11/ 2016ዓ፣ም የትምህርት ሳምን ሆኖ ይከበራል፡፡ መስከረም 14 2016 ዓ.ም የአንደኛው ወሰነ ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት ይጀምራል፡፡ በዚሁ ቀን የራድዮ እና የቴሌቪዥን ሥርጭት ይጀምራል፡፡

ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016ዓ.ም የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት የማጠቃላያ ፈተና ይሰጣል፡፡ ከየካቲት 4 እስከ 8/2016 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት፣ ውጤት የሚጠናቀርበት እና የሚገለጽበት ጊዜ ይሆናል፡፡

የካቲት 10 /2016ዓ.ም ወላጆች እና የትምህርት ማኅበረሰብ በተገኙበት የአንደኛው ወሰነ ትምህርት ውጤት መግለጫ ይሆናል፡፡

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሁለተኛው ወሰነ ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት ይጀምራል፡፡ የራድዮ እና የቴሌቪዥን ሥርጭት ይጀምራል፡፡

ከግንቦት 12 ቀን እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠቃለያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል፡፡ ከግንቦት 26 እስከ 30 /2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ይሰጣል፡፡

ከሰኔ 3 እስከ 7 /2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ይሰጣል፡፡

ከሰኔ 17 እስከ 21/ 2016 ዓ.ም የሁለተኛው ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ የፈተና ጊዜ ይሆናል፡፡

ከሰኔ 24 እስከ 28 2016 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት፣ ውጤት የሚጠናቀርበት እና የሚገለጽበት ጊዜ ይሆናል፡፡

ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ወላጆች እና የተምህርት ማኅበረሰብ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል፡፡

ዘጋቢ ፦ ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአማራ ክልል የወባ በሽታ ሥርጭት እና የሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው” የአማራ ክልል ጤና ቢሮ
Next articleበደሴ ከተማ ከ64 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ የትምህርት መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና ሥራ ተካሄደ።