የፌደራል ፖሊስ ተቋማዊ አቅሙ እና አሕጉራዊ እውቅናው እያደገ መሆኑን አስታወቀ።

29

አዲስ አበባ፡ መስከረም 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል ፖሊስ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ግዳጅን ለፈፀሙ አባለቱ እና የሥራ ክፍሎች እውቅና እየሰጠ ነው።

በዚህ የእውቅና መርሐግብር ላይ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ነብዩ ዳኘ ባደረጉት ንግግር ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ጠንካራ ተቋም ለመሆን ችሏል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ፖሊስ ከሕዝብ ጋር ተቀራርቦ የሚሠራ እና የመፈፀም አቅደሙን በማሳደግ የምርምር እና የወንጀጀል ምርመራ አቅሙን ያሳደገ የፖሊስ ሠራዊት መገንባት ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት አሕጉራዊ፣ ክፈለ-አሕጉራዊ እና የውጭ ሀገራት ሽልማቶችን መውሰድ የቻለ ጠንካራ ተቋም ለመሆን መብቃቱን አንስተዋል።

የፌደራል ፖሊስ ተቋማዊ አቅሙ እያደገ የመጣ የፀጥታ ተቋም ሆኗል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜን ወሎ ዞን 25 የግንባታ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ለምረቃ ዝግጁ ማድረጉን የዞኑ አልማ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
Next articleየአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የኮሌራ ክትባትን አስጀመሩ።