
ባሕር ዳር: መስከረም 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ በ12ኛ ዙር አጭር ኮርስ ያሰለጠናቸውን የመገናኛ አመራር ሠልጣኞች አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ በመከላከያ ሠራዊት የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ የኮሌጁ አዛዥ ኮሎኔል አራጋው መሃመድ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት መኮንኖችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ለምርቃት የበቁት የመገናኛ አመራር ሰልጣኞች የሠራዊቱን የውጊያ ድጋፍ በአስተማማኝ ሁኔታ መስጠት የሚያስችል ትምህርትና ሥልጠና ሲከታተሉ መቆየታቸው ተገልጿል።
የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ኮሌጅ የመገናኛ ትምህርት ቤት በሚል ሥያሜ በ1953 ዓ.ም ተመስርቶ በራዲዮ ጥገና፣ በማዞሪያ ስልክ ኦፕሬተር፣ በጄኔሬተር ኦፕሬተር፣ በሞርስ ኦፕሬተር፣ በቴሌፎን ኦፕሬተርና በታይፒስት ሥራ እንደጀመረ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓትም በኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ፣ በኢንፎርሜሽን ሴኪዩሪቲ እና በማኔጅመንት ትምህርት ክፍሎች በዲግሪ፣ በዲፕሎማ፣ በመካከለኛ፣ በአጭር ኮርስ፣ በሰልጥኖ አሰልጣኝ፣ በሪፍሬሽመንት፣ ለሲቪሎች በድጋፍና በሰርተፊኬት ለውጭ ሰልጣኞች ትምህርትና ሥልጠና በመሥጠት በመከላከያ ሠራዊት ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የሚመራ ተቋም ነው። መረጃው የኢዜአ ነው::
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!