
ባሕርዳር፡ መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሳውዲ አረቢያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በትምህርት እና ሥልጠና፣ የእግር ኳስ ልማት እና ትብብር ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ስምምነት በሪያድ ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እና የሳውዲ አቻቸው ያስር አል-ሚስሀል ናቸው።
የስምምነቱን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚገለጽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ፌዴሬሽኑ ከዚህ ቀደም ከሞሮኮ ሮያል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት ባሳለፍነው ዓመት በመፈራረም የጋራ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!