የአማራ ክልል ለሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳደር የተለያዩ ተቋማት የመሪዎች ሹመት ሰጠ።

58

ባሕር ዳር: መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል መንግሥት በየደረጃው የሚገኙ መሪዎችን በአዲስ ምደባ እንደሚደረግ በገለጸው መሠረት የመሪዎች ምደባ በመከናወን ላይ ነው።

ለሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳደር የተለያዩ ተቋማትም ክልሉ የመሪዎች ምደባ አድርጓል።
በዚህም መሰረት
1.አቶ ዳዊት ኀይሉ – የገንዘብ መምሪያ ኀላፊ
2.አቶ አስቻለው ግዛቸው – የሰላም ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኀላፊ
3.አቶ ምትኩ ማሙሽ – የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ
4.አቶ ፀጋዬ እንግዳወርቅ – የትምህርት መምሪያ ኀላፊ
5.አቶ ደምሰው መንበሩ – የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ
6.አቶ ሰለሞን አልታየ – የሚሊሻ ኀላፊ
7.አቶ ታደሰ ማሙሻ – የግብርና መምሪያ ኀላፊ
8.አቶ ሰለሞን ቀለሙ – የግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ
9.አቶ ደምሴ አርአያ -የገቢዎች መምሪያ ኀላፊ
10.አቶ ሳሳሁ ጌታ -የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ
11.አቶ መሐመድ አህመድ – የመንገድ መምሪያ ኀላፊ
12.አቶ ዘውገ ንጉሴ – የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ
13.አቶ ደጀኔ በቀለ -የትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ
14.አቶ ብርሃን ጨርቆስ – የሥራና ሥልጠና መምሪያ ኀላፊ
15.ወ/ሮ ሃይማኖት ዝቁ -የባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ
16.ሲ/ር እታይዘሩ ጌታነህ -ሱፐርቪዥን ጥናትና ምርምር ምክትል አማካሪ
17.ወ/ሮ ትዕግስት አግዴ – የወጣቶች ጉዳይ ዋና አማካሪ በመኾን መሾማቸውን ከሰሜን ሸዋ ዞን አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል መንግሥት ለደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳደር ለ20 መሪዎች ሹመት ተሰጠ፡፡
Next articleበአዲስ አበባ እና ጋምቤላ ክልል ለሚካሄዱ የአጀንዳ ልየታ መድረኮች ተወካዮችን የመለየት ሥራ ሊጀመር መኾኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ።