አዲሱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ልዩ ልዩ ሹመቶችን ሰጡ።

187

ባሕርዳር፡ መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው እለት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተሾሙት አቶ ጎሹ እንዳላማው ልዩ ልዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በአዲስ የተሾሙ የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር አመራሮችም፦

👉አቶ አስሜ ብርሌ – የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ
👉አቶ ተሻገር አዳሙ- የባሕር ዳር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ
👉አቶ አደራ ጋሼ -የባሕር ዳር ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ ኃላፊ
👉አቶ ጌትነት አናጋው -የባሕር ዳር ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ
👉ወይዘሮ መልካምሥራ ካሳው -የባሕር ዳር ከተማ መሬት አሥተዳደርና አጠቃቀም መምሪያ ኃላፊ
👉አቶ ዘመነ አሰፋ -የባሕር ዳር ከተማ ሥራና ስልጠና መምሪያ ኀላፊ
👉ወይዘሮ ሰብለ ዘውዱ – የባሕር ዳር ከተማ ሴቶች ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
👉 ወይዘሮ ዓለም አሰፋ የባሕር ዳር ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ ኾነው ተሹመዋል።

ዘጋቢ :-ጋሻው አደመ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዓለም ደረጃ በወባ በሽታ ስርጭትና ሞት ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የአፍሪካ አህጉር ነው” አፍሪካ አቀፍ የወባ ቁጥጥር ማኅበርና ጤና ሚኒስቴር
Next articleለ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች የኮሌራ ክትባት መቅረቡን የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡