የውኃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ።

53

👉ከ60 እስከ 80 በመቶ ተላላፊ በሽታዎች በውኃ ወለድ የሚከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል።

ባሕር ዳር: መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር ዓቀፍ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኤግዚቢሽን የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በሳይንስ ሙዝየም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የውኃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ በውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውኃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገልጸዋል።

ከ60 እስከ 80 በመቶ ተላላፊ በሽታዎች በውኃ ወለድ የሚከሰቱ በሽታዎች መኾናቸውን ክቡር አምባሳደሩ ገልጸው፤ በመጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የውኃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት ለመከላከል እየተሰራ ነው ብለዋል።

የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን በከተማ እና በገጠር በአማካይ ከ60 – 70 በመቶ መድረሱን ገልጸው የሳኒቴሽን አገልግሎት በ2030 የዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ አምባሳደሩ ገልጸዋል። መረጃው የውኃና ኢነርጅ ሚንስቴር ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በ2015 የምርት ዘመን ከ393 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል” ግብርና ሚኒስቴር
Next articleአቶ ጎሹ እንዳላማው ወንድምአገኝ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።