የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ መሪዎች ሥልጠና ተጀመረ።

284

ባሕር ዳር: መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ መልእክት ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎች የተዘጋጀ የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።

የሥልጠናው አላማ ከፍተኛ መሪዎች ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ኹኔታዎችን ተገንዝበው ፤ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ፓርቲው ለሕዝቡ የገባውን ቃል ማስፈጸም የሚያስችል የአመራር አቅም እንዲፈጥር ያለመ መኾኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ገልጸዋል።

በሥልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ከፍተኛ መሪዎች እየተሳተፉ መኾኑን ከፓርቲው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአቶ ደመቀ መኮንን በቡድን 77 እና የቻይና መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኩባ ገቡ
Next article“በ2015 የምርት ዘመን ከ393 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተገኝቷል” ግብርና ሚኒስቴር