አቶ ደመቀ መኮንን በቡድን 77 እና የቻይና መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኩባ ገቡ

75

ባሕር ዳር: መስከረም 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቡድን 77 እና የቻይና መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የኩባ ዋና ከተማ ሃቫና መግባቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

አቶ ደመቀ እና ልዑኩ ጆሴ ማርቲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች እና በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው ጉባኤው የወቅቱን የልማት ተግዳሮቶች ለመፍታት የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ሚና ላይ የሚያተኩር መኾኑ ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ 307 ታዳጊዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መዘጋጀቱን አስታወቀ።
Next articleየብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ መሪዎች ሥልጠና ተጀመረ።