ብሪታንያ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ አደረገች።

61

ባሕርዳር፤ መስከረም 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉ በብሪታንያ ቀይ መስቀል እና በኔዘርላንድስ ቀይ መስቀል ማኅበር የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚታገዝ ተመላክቷል፡፡
ድጋፉ በጤና፣ ንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት እና ንጽሕና አጠባበቅ ላይ ትኩረት ላደረጉ ፕሮጀክቶች የሚውል ነው ተብሏል።

ለፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የስምምነት ሰነድ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልሽ መካከል ተፈርሟል። ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ፓውንዱ በገንዘብ የቀረበ ሲሆን፤ ቀሪው ደግሞ ለቴክኒክ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፋና እንደዘገበው በመርሐ ግብሩ የቴክኒክ ድጋፉ አካል የሆኑ የ10 ተሽከርካሪዎች ርክክብ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የ104 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ።
Next article“የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳደር እና የደሴ ከተማ ሕዝብ ለመከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ለሠራዊቱ ተጨማሪ የሞራል ድጋፍ ኾኖታል” ብርጋዴር ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ