
ባሕር ዳር: መስከረም 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ።
በውይይቱም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ በሸዋሮቢት፣ በጎንደር፣ በኮምቦልቻ እና በባህር ዳር በወንጀል ተጠርጥረው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ በህግ ጥላ ስር ያዋሉትን ተጠርጣሪዎች በጎበኘበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ባነሷቸው ሀሳቦች ዙርያ ቦርዱ ምክረ ሀሳብ ለእዙ በማቅረብ ውይይትና ምክክር ማድረጋቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!