የጎንደር ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤው ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ።

177

ጎንደር: መስከረም 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የጎንደር ከተማ ምክር ቤት የ4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ሲያካሂድ የሥራ ኀላፊዎችን ሹመት ከማጽደቅ በተጨማሪ የከተማ አሥተዳደሩን የ2016 ዓ.ም በጀት መርምርም አጽድቋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ ከተማው አሁን ያለውን ወቅታዊ ኹኔታ የሚመጥኑ የአመራር ብቃት ያላቸው መሪዎች ሊኖሩት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ስለኾነም ሹመት መስጠት ተገቢ ኾኖ መገኘቱን አስታውቀው ለምክር ቤቱ እጩ ተሿሚዎችን አቅርበዋል።
ተሿሚዎች ያላቸውን የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድ ፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ሙያዊ ብቃት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እጩዎቹን አቅርበው አፀድቀዋል።
በዚህም መሠረት፡-

👉 አቶ ደብሬ የኋላ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ

👉 አቶ ግርማይ ልጅአለም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ

👉 ኮማንደር አሰፋ ሸቤ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ ዮናስ ይትባረክ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ባሕል ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ ሰኢድ የሻው የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ

👉 ወይዘሪት ውብአካል ቢራራ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሴቶች ሕፃናት መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ አበራ ደባስ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ ማሩ ሙሀመድ ያሲን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ ወንዳቸው ሥራው አለሜ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ፍትሕ መምሪያ ኀላፊ

👉 አቶ ፋሲል አብዩ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሲቪል ሰርቪስና የሰው ኀይል መምሪያ ኀላፊ ኾነው እንዲሾሙ አቅርበው ምክር ቤቱ የቀረቡ እጩዎችን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

👉 በጉባኤው ወይዘሮ እናትነሽ ዋለ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ኾነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል የጎንደር ከተማ ምክር ቤት የ4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የ2016 የበጀት ዓመት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሥራዎች ማስፈፀሚያ በጀትን አፅድቋል።

በዚህም 2 ቢሊየን 755 ሚሊዮን 740 ሺህ 513 ብር የ2016 በጀት ዓመት ጥቅል በጀት ኾኖ ፀድቋል።

ዘጋቢ፡- ቃልኪዳን ኃይሌ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዲጂታል የተማሪዎች መለያ ሥርዓት ተግባራዊ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሰታወቀ።
Next articleመርማሪ ቦርዱ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ውይይት አደረገ።