“አዲሱ ዓመት ፍትሕን በመከተል ለሰብዓዊነት እና ለሰላም የምንቆምበት ሊኾን ይገባል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው

65

ባሕር ዳር: መስከረም 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው የአዲስ ዓመት መልእክት አስተላልፈዋል። “እኛ በዘመን ጅረት ውስጥ ደራሾች ነን፣ ዓመታት በተቀያየሩ ቁጥር ለመጭው ትውልድ የሚበጅ አዳዲስ ሥራዎችን ማከናወን የዘወትር ተግባራችን ሊኾን ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ አሸተ “በአዲሱ ዓመት በእውነት ላይ የተመሰረተ የፍትሕን መንገድ በመከተል ለሰብዓዊነት እና ለሰላም የምንቆምበት ሊኾን ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል። መጭው ጊዜ ሀገራችን ከግጭት እና አለመረጋጋት በዘላቂነት የምትወጣበት፣ የዜጎችን መፈናቀል እና ግድያ የማንሰማበት የክብር ዓመት እንዲኾን እመኛለሁ ነው ያሉት በመልእክታቸው።

“መጭው አዲስ ዓመት ለአማራ ሕዝብ እና ለመላው ኢትዮጵያዊያን ብሩህ እና የለማች ሀገር ለመሥራት ተስፉ የሚሰነቅበት ይኹን” ሲሉም ገልጸዋል።

ልማት ወዳድ የኾነው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብ ሰፊ የኾነውን የዞኑ ተፈጥሯዊ ጸጋ በማልማት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥበት ዓመት እንዲኾንም አቶ አሸተ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አዲስ ዓመትን አከበሩ።
Next article“በ2016 ዓ.ም በሕዳሴው ግድብ አምስት ተጨማሪ ዩኒቶችን ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ ነው” ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ