በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አዲስ ዓመትን አከበሩ።

58

መስከረም: 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አዲስ ዓመትን በየሀገራቱ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና በቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አከበሩ።

የ2016 አዲስ ዓመት (ዘመን መለወጫ) በዓል ከተከበሩባቸው ካሉ ሀገራት መካከል አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጅቡቲ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚቶች፣ ስዊዘርላንድ፣ ጃፓንና ደቡብ ሱዳን ይጠቀሳሉ።

በዓሉን ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተለያዩ መርሐ ግብሮች በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አክብረዋል።

በሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ አምባሳደሮች ለመላ ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተለይም ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ ለጀመረቻቸው ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ስኬት እያደረጉ ያለውን ድጋፍ በአዲሱ ዓመትም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንም የመልካም ምኞች መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጎንደር ከተማ አሥተዳደር አመራሮች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላትና መሪዎች የአዲስ ዓመት በዓልን በጋራ አክብረዋል፡፡
Next article“አዲሱ ዓመት ፍትሕን በመከተል ለሰብዓዊነት እና ለሰላም የምንቆምበት ሊኾን ይገባል” የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው