የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አመራሮች እና የመከላከያ ሠራዊት አባላትና መሪዎች የአዲስ ዓመት በዓልን በጋራ አክብረዋል፡፡

41

ጎንደር: መስከረም 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዓላትን በጋራ ከማክበር ባለፈ በ2015 ያጋጠሙ የጸጥታ ችግሮችን በ2016 ውይይቶችን በማድረግ መፍታት እንደሚገባ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባና የኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ባዩ አቡሀይ ገልጸዋል፡፡

2016 ዓመተ ምህረት ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር መሥራት እንደሚገባ የገለጹት አቶ ባዩ የሕዝብ ጥያቄዎች ተፈትተዉ ወደፊት እንድንሻገር መስራት የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት ለሰላም እንደሚሰራ የገለጹት የመከላከያ ሰራዊት 504ኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ማርየ በየነ ካለንበት የጸጥታ ችግር በመውጣት ወደ መደበኛ ግዳጃችን የምንገባበት ዓመት መሆን አለበት ብለዋል። ጥያቄዎችን በውይይት ለመፍታት ሁሉም አካላት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸዉ ብርጋዴር ጀነራሉ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ደስታ ካሳ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአርባ ስምንት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጭ የተለያዩ የበጎ አድራጎት እና የልማት ሥራዎች ማከናወኑን የባሕር ዳር በጎ አድራጎት ማኅበር አስታወቀ።
Next articleበተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አዲስ ዓመትን አከበሩ።