
ጎንደር: ጳጉሜ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር እና የጎንደር ከተማ አሥተዳደር በጋራ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ 19 የቀንድ ከብቶችን እንዲሁም ተጨማሪ በግና ፍየሎችን ለመከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል።
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሐይ ሕዝቡ በፀጥታ መዋቅሩ ያገኘው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በማሰብ ስጦታው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት መበርከቱን ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አላምረው አበራ ለአዲስ ዓመት ለመከላከያ ሠራዊት ያለንን ድጋፍ ለማሳየት እገዛ መደረጉን ገልጸዋል።
በርክክቡ ወቅት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኙት ብርጋዴል ጄኔራል ማርየ በየነ ሠራዊቱ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሕዝብ ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለው ለተደረገው እገዛ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ምሥጋናው ከፍያለው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!