
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲሱ ዓመት የሠላምና የደስታ እንዲሆን በመመኘት ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመላው የሀገቱ ህዝቦች፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና ደጋፍዎች እንኳን ከ2015 ዓ.ም ወደ 2016 ዓ.ም አሸጋገራችሁ ብሏል::
በአዲሱ ዓመት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በመንግሥትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አብሮ የመስራት የፖለቲካ ባሕል የሚዳብርበት እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር የጋራ ምክር ቤቱ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግም ጠቅሷል።
“2016 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሠላምና መረጋጋት የሚፈጠርበት የሠላም፣ የደስታና ተድላ ዓመት እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ ይመኛል” ብሏል። ዘገባው የኢዜአ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!