እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ

96

በፈጣሪ ቸርነት 2015ን አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ኢትዮጵያ በውጣ ውረድ ውስጥ እያሸነፈች ተጉዛለች።

ጽኑ መርሕ፣ ብርቱ ሕዝብና የማይሸነፍ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል።

ብዙ ነገሮችን አሳክተናል፤ አያሌ ፈተናዎችን በድል ተወጥተናል፤ እልፍ መሰናክሎች ቢደረደሩም ጠንካራ መሰረት ሆነውን አልፈዋል።

የተሳኩልን ሁሉ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ውጤቶች ናቸው።

የተፈተንባቸው ደግሞ በመለያየት የተነሣ የመጡ ናቸው። በቀጣዩ ዓመት ፈተናዎቻችን እጅግ ቀንሰው፤ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ከአልማዝ ጠንክሮ፤ የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በጽኑ መሠረት ላይ እናጸናዋለን።

ልማትና ብልጽግናዋን ወደሚመጥናት ደረጃ እናሻግረዋለን።

አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም

Previous articleውይይትን የችግሮች መፍቻ አይነተኛ መሳሪያ አድርጎ የመጠቀም ልምድን ማዳበር ተገቢ መኾኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ገለጸ፡፡
Next articleበተስፋው ምድር አዲስ የተስፋ ዘመን ነጋሪት በአዲስ ዓመት ይጎሰማል!