ውይይትን የችግሮች መፍቻ አይነተኛ መሳሪያ አድርጎ የመጠቀም ልምድን ማዳበር ተገቢ መኾኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ገለጸ፡፡

31

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ አዲሱ ዓመት ፍቅር እና አንድነት የሚገዝፍበት፤ ችግር እና የሰላም እጦት ፈፅሞ የማይሰሙበት እንዲኾን የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ያሳለፍነው ዓመት የሰሜን ሸዋ ዞን በተለያዩ የችግር እና የሰላም እጦት ሲፈተን እንደነበር ያነሱት የዞኑ አሥተዳደሪ አዲስ ዓመትን ስናከብር የነበርንበት የሰላም እጦት ወደ ተሟላ ሰላም እንዲመለስ ሁላችንም እራሳችንን የምናሳርፍበት የሃሳብ ስንቅ የምንሰንቅበት ሊኾን ይገባል ብለዋል፡፡

በብዙዎች ትብብር የተመለሰው ሰላም እንዳይቀለበስ በአዲሱ ዓመት ችግሮች ሲገጥሙ ውይይትን አይነተኛ መሳሪያ አድርገን የመጠቀም ልምድን ማዳበር ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡

አዲሱ ዓመት ፍቅር እና አንድነት የሚገዝፍበት ችግርና የሰላም እጦት ፈጽሞ የማይሰሙበት እንዲሆን ዋና አሥተዳዳሪው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፋብሪካው ከተመሰረተ ጀምሮ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጥቷል” የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ
Next articleእንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ