
ባሕር ዳር: ጳጉሜ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕልና የስፖርት ሚኒስቴር የአብሮነት ቀንን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ ይገኛል።
የባሕልና የስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ እንደገለጹት የአብሮነት ቀን ሲከበር የጋራ እሴቶችን በማጽናትና በማስቀጠል ሊኾን ይገባል።
ሚኒስትር ዲኤታዋ ቀኑ ሲከበር ቀደምት አባቶች የተለያየ ባሕል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ያላት ሀገርን አጽንተዉ አቆይተዋልና ይህን ለማስቀጠል መኾን አለበት ብለዋል።
ባለፋት ጊዜያት ኢትዮጵያን ሊያጠቁ የሚፈልጉ የውጭም የውስጥም ኀይሎች በአብሮነት ተረተዋል ያሉት ወይዘሮ ወርቅነሽ፤ በቀጣይም ሀገሪቱ የሚያጋጥሟትን ችግሮችን በአብሮነት መንፈስ በመስበር ሀገሪቱን ማሻገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ ብዝሐነት ባለባት ኢትዮጵያም ያንዱ ማንነት አንዱ በማክበር የሰላም ፣ የአብሮነት ፣ የፍቅር እሴቶች ማጎልበት ያስፈልጋል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!