
ባሕር ዳር: ጳጉሜ 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሃይማኖት አባቶቹ የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
አዲሱ ዓመት ራስን ለመለወጥ፣ ለሀገር እና ለወገን መልካም ተግባራትን ለማከናወን ምዕመኑ በትጋት የሚሠራበት ሊሆን እንደሚገባ ነው የሃይማኖት አባቶቹ በመልዕክታቸው ያሳሰቡት።
የተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ መልካም ተግባራት የተከናወኑበት፣ በአንፃሩም በርካታ ተግዳሮቶች የተስተዋሉበት መሆኑን አስታውሰው፣ የተገኙ መልካም ውጤቶች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።
ይሁንና በኢትዮጵያ የተስተዋሉ ግጭቶች እና አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት ሊሠሩ ይገባል ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በዓሉንም፣ በተለያየ ምክንያት ችግር የደረሰባቸውን ወገኖች በመርዳት እና በመንከባከብ አብሮ ማሳለፍ እንደሚገባም፣ የሃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
