
የጎንደር ከተማ ወጣቶች በአካባቢ ጽዳት የበጎ አድራጎት ሰራዎችን እያከናወኑ ነው።
የጎንደር ከተማ ወጣቶች ከተማቸውን አስውበው እንግዶቻቸውን ለመቀበል ከማለዳው 12 :30 ጀምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን እያፀዱ ይገኛሉ።
ከከተማዋ የተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ወጣት ሰራተኞችም በጋራ ሆነው ሲያጸዱ ተመልክተናል።
ወጣቶቹ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አደረጃጀት ፈጥረው ተግባራትን ለማስተባበር እና ባህላቸውን በስነ ስርዓት ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆናቸውንም ለአብመድ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ኃይሉ ማሞ