ወጣቶች ጥንት አባቶቻቸው ያቆዩላቸውን አንድነት እንዲያጠናክሩ የኢትዮጵያ አረጋውያን ማኅበር አባቶች ጠየቁ፡፡

57

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፍትሕ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት የትውልድ ቀን በዓል ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ አባት አርበኞች፣ አረጋዊያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ጳጉሜን 5 የትውልድ ቀን ”ኢትዮጵያ የትውልዶች ድምር” በሚል መሪ ሃሳብ በፌደራል ደረጃ እየተከበረ ይገኛል፡፡

የትውልድ ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አረጋውያን ማኅበር አባቶች ለወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት ያለፈው ትውልድ ለሀገር ዳር ድንበር በጋራ ተፋልመው ነጻነቷን ያስጠበቋት በአንድነት እና በመተባበር እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድም ከግጭት ወጥቶ የፍቅር፣ የሰላም፣ የመረዳዳት፣ የመደጋገፍ እና የመከባበር እሴቶችን በማዳበር እና የጥንት አባቶችን የአንድነት መንፈስ በማጠናከር የበለጸገች ሀገርን ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ታሪካዊ አደራ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

አሁን የሚታዩ የግብረ ገብ ችግሮችን ከቤተሰብ ጀምሮ የእምነት እና የመንግሥት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአራተኛና የመጨረሻ የውኃ ሙሌት ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች፦
Next article“ኢትዮጵያ ተባብረን ከሠራን ተስፋ ያላት ሀገር ናት” ፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ