
👉የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
👉በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
👉ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል።
👉ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር።
👉 በውስጥ ፈተና በውጭ ጫና ነበረብን።
👉የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም።
👉ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
