“የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

53

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን በዛሬው እለት አብስረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውኃ ሙሌቱን በማስመልከት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ተከታዩን መልእክት አስተላልፈዋል፦

የሕዳሴው ግድብን አራተኛና የመጨረሻ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረን በመሥራታችን ፈጣሪ ረድቶናል። በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በጸሎታቸው በሥራው ውስጥ የተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህ ኅብረታችን በሌሎች ጉዳዮቻችንም ሊደገም ይገባዋል።

ብዙ ፈተና ነበረው፤ ወደኋላ እንድንመለስ ብዙ ተጎትተን ነበር። በውስጥ ፈተና በውጭ ጫና ነበረብን። ከፈጣሪ ጋር የመጣውን ሁሉ ተቋቁመን ለዚህ ደርሰናል። ነገር ግን የዳገቱ ጫፍ ላይ ደረስን እንጂ ዳገቱን ወጥተን አልጨረስነውም። በቀጣዩ ጊዜ ያቀድነውን አጠናቅቀን ፈጣሪን እንደምናመሰግን እምነቴ ነው። ለግድቡ የምናደርገውን ማናቸውንም ድጋፍ እስከ ፍጻሜው እንድንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቀጣይነት እየገነባነው የምንሄደው ትውልድ ኢትዮጵያዊነቱን ከአፍሪካዊነቱ፣ አፍካዊነቱን ከዓለም አቀፋዊነቱ ያጣመረ ሊሆን ይገባል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Next article“እኛ ከእኛ የተሻለ ትውልድ መፍጠር ካልቻልን ሀገር እየገደልን ነው” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ